የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ
አሶሳ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 2ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቋል።
ምክርቤቱ በዛሬ ውሎው የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ሪፖርት በማድመጥ አጽድቋል።
በመቀጠልም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር አደረጃጀትና የመስኖ አውታር አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸደቀ ሲሆን አዋጁ ዘላቂነት ያለው የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን ለማጎልበት እና የመስኖ አውታሮችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያግዝ መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል።
በተጨማሪም አርሶአደሩ በመስኖ እርሻ እያከናወነ በሚገኘው የግብርና ስራ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አዋጁ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ተነስቷል።
ምክር ቤቱ የክልሉን ፍትህ ቢሮ ማቋቋሚያ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ያፀደቀ ሲሆን በዲስፒሊን እና ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ምክንያት ከዳኝነት የተሰናበቱ ዳኞችን ስንብትም ተቀብሎ አጽድቋል።