ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እንግዶቿን በክብር እየሸኘች ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና በ2ኛው የጣሊያን-አፍሪካ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ መሪዎች በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ በስኬት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው።

በዚህም የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ፣ የናሚቢያ ፕሬዝደንት ኔቱምቦ ናንዲ ንዴትዋ፣ የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ በቦሌ ዓለም-አቀፍ አየር ማረፊያ የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።


 

እንዲሁም የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት መሐመድ ጃሎው እና የሲሼልስ ምክትል ፕሬዝዳንት ሴባስቲን ፒሌይ በቦሌ ዓለም-አቀፍ አየር ማረፊያ የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።


 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለእንግዶቹ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።


 

የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች https://linktr.ee/ENADigital

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም