ቀጥታ፡

አርሰናል በኤፍኤ ካፕ ወደ አምስተኛ ዙር አለፈ 

አዲስ አበባ ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ-ግብር አርሰናል ዊጋን አትሌቲክን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኖኒ ማዱዌኬ፣ ጋብርኤል ማርቲኔሊ፣ ጋብርኤል ጄሱስ እና የዊጋን አትሌቲኩ ጃክ ሃንት በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። 

በጨዋታው ላይ አርሰናል ከፍተኛ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።

ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ያቀበለው ኤበረቺ ኤዘ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል ወደ አምስተኛ ዙር አልፏል። 

አርሰናል የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን 14 ጊዜ በማንሳት ስኬታማው ክለብ ነው።

በሊግ ዋን የሚገኘው የአንድ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ዊጋን አትሌቲክ የኤፍኤ ካፕ ጉዞው አራተኛ ዙር ላይ ተገቷል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ፉልሃም፣ ሊድስ ዩናይትድ፣ ሰንደርላንድ እና ዎልቭስ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ አምስተኛ ዙር አልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም