39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፤የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቋል።
ጉባኤው የተካሄደው” ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
መሪዎቹ 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ውይይት ባደረገባቸው አጀንዳዎች ላይ መክረዋል።
የውሃ ደህንነት እና የንጽህና አጠባበቅ፣የአጀንዳ 2063 ትግበራን እና አህጉራዊ ትስስር፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣የሰው ኃይል ልማት፣ተቋማዊ እና የፋይናንስ ሪፎርሞች፣ ቀጣናዊ አጋርነት እና አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና ከተመረከባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።