እንግሊዝ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የሚያስችል አዲስ ስልት ተግባራዊ አድርጋለች - ኢዜአ አማርኛ
እንግሊዝ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የሚያስችል አዲስ ስልት ተግባራዊ አድርጋለች
አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፡- እንግሊዝ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነት ማጠናከር የሚያስችል አዲስ ስልት ተግባራዊ ማድረጓን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች ለፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ (ፒኦኤ) እንዳሉት፤ እንግሊዝ ከአፍሪካ አህጉር ጋር የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ጥልቅ ወዳጅነትን መገንባት ትፈልጋለች፡፡
የጠንካራ አፍሪካ መኖር ለአፍሪካ አህጉር ልቀት ብቻ ሳይሆን ከእንግሊዝ ጋር ለሚኖራት ቀጣይነት ያለው ዘላቂ ግንኙነትና የጋራ ተጠቃሚነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንግሊዝ ከአፍሪካ አህጉር ጋር ያላትን የጋራ ተጠቃሚነትና ትብብርን ማጠናከር እንደምትፈልግም ተናግረዋል፡፡
ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ከተለየያ የዓለም ማዕዘናት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ተሳታፊዎች ግባቸው ከአፍሪካ ህብረት ጋር የባለብዙ ወገን ጥልቅ ትብብር ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንግሊዝ ከአፍሪካ ጋር ወዳጅነትን ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸው፤ ከለጋሽና ተቀባይ ግንኙነት ወደ ሚዛናዊና ተመጣጣኝ ትብብር መምጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
እንግሊዝ የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063ን ለመደገፍ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኑን ጠቅሰው፤ የአህጉሪቱ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ አካታች እድገትና ዘላቂ ልማት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር እንግሊዝ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ግንኙነቷን በማጠናከር ጥልቅ ወዳጅነትና ዘላቂ ትብብር ትፈልጋለች ብለዋል፡፡
ከአፍሪካ ጋር ገቢራዊ ያደረግነው የትብብር ስልት በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ እያደገ የመጣውን የአፍሪካ ሚና እውቅና የሚሰጥና ለአፍሪካ ተኮር ኢኒሼቲቮች ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንግሊዝ ለአየር ንብረት ለውጥ በማይበገር ኢኮሚያዊ ዕድገት እና ሰላምና ደህንነት መስኮች በጋራ ለመስራት ያላትን ዝግጁነት ያሳያል ብለዋል፡፡
የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች
https://linktr.ee/ENADigital