ማንችስተር ሲቲ በኤፍኤ ካፕ ወደ አምስተኛ ዙር አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ በኤፍኤ ካፕ ወደ አምስተኛ ዙር አለፈ
አዲስ አበባ ፤ የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ ሳልፎርድ ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማርክ ጌሂ እና የሳልፎርድ ሲቲው አልፊ ዶሪንግተን በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አዲስ ፈራሚው ማርክ ጌሂ በሲቲ ማልያ የመጀመሪያ ጎሉን አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ወደ አምስተኛ ዙር አልፏል።
በሊግ ቱ(አራተኛ ዲቪዚዮን) የሚገኘው ሳልፎርድ ሲቲ የኤፍኤ ካፕ ጉዞው አራተኛ ዙር ላይ ተገቷል።