ጥቂት ስለ አዲሱ አፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ - ኢዜአ አማርኛ
ጥቂት ስለ አዲሱ አፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ
ጥቂት ስለ አዲሱ አፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
“ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው።
በጉባኤው የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና የአንጎላ ፕሬዝዳንት ጆአኦ ሎሬንዞ ሊቀመንበርነታቸውን ለብሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ አስረክበዋል።
አዲሱ ሊቀመንበር እና የብሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ከእ.አ.አ ጁን 2020 አንስቶ ሀገሪቷን በርዕሰ ብሔርነት እየመሩ ይገኛሉ።
ንዳይሺሚዬ ፕሬዝዳንት የሆኑት እ.አ.አ በ2020 ፕሬዝዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ነው።
የብሩንዲው ፕሬዝዳንት እ.አ.አ ጁን 17 1968 በማዕከላዊ ብሩንዲ ጊቴጋ ግዛት ጊሄታ የተባለ ስፍራ ነው የተወለዱት።
10ኛው የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ የብሩንዲ ብሄራዊ ወታደራዊ ኃይል ምክትል ዋና አዛዥ፣ የፕሬዝዳንት የመከላከያ እና ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ እና የሀገር ውስጥ ጉዳይና የህዝብ ደህንነት ሚኒስትር በመሆን ሰርተዋል።
በተጨማሪም የፕሬዝዳንት ከፍተኛ አማካሪ እና የብሩንዲ ገዢ ፓርቲ የብሄራዊ የዴሞክራሲ ጥበቃ ምክር ቤት (CNDD-FDD) ዋና ፀሐፊ በመሆንም አገልግለዋል።
ፕሬዝዳንት ንዳይሺሚዬ በቀጣናው ዲፕሎማሲ ቀጣናዊ ትስስር መጠናከር ላይ በመሞገት ላይ ጠንካራ ተሟጋች ናቸው።
ብሄራዊ መረጋጋት፣ ኢኮኖሚያዊ ልማት እና የፖለቲካ መረጋጋት ማስፈን የመንግስታቸው አበይት አጀንዳዎች ናቸው።
የአፍሪካ ህብረት የ2026 ሊቀ መንበር ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ የአፍሪካን የፖሊሲ የትኩረት መስኮች ትግበራን ያስተባብራሉ።
ንዳይሺሚዬ በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት ለአንድ ዓመት ያገለግላሉ።