ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ለሶስተኛ ጊዜ የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ለሶስተኛ ጊዜ የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት እያልኩ የተሰማኝን ደስታ እገልጻለሁ ብለዋል።
የባርቤዶስ ሕዝብ ላደረገው ስኬታማ የዴሞክራሲ ልምምድ አድናቆታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞትሊ ለባርቤዶስ ሕዝብ እድገት፣ ብልጽግና እና ዘላቂ ልማት ለሚያደርጉት ጥረት መልካም እድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።
በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር እና ትብብራችንን ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።