ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ ጋር በዘላቂ ልማትና በአፍሪካ የልማት ቅድሚያ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ከፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ ጋር መወያየት ሁልጊዜም አስደሳች ነው!" ያሉ ሲሆን፣ ውይይቱ ባለፈው ዓመት ከነበራቸው ቆይታ የቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል።
በምክክራቸውም በዘላቂ ልማት፣ በኢኮኖሚ ዕድገት እና ለአፍሪካ ልማት መሰጠት በሚገባቸው የቅድሚያ ጉዳዮች ማተኮሩን አስታውቀዋል።