ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሲዲ ኡሉድ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሲዲ ኡሉድ ጋር በቡድን 20 ስብሰባ ወቅት ከነበረን ውይይት የቀጠለ ምክክር አድርገናል ብለዋል።
ውይይታችን በአካታች እድገት ድጋፍ፣ በልማት ፋይናንስ እና በመላው አፍሪካ ስለሚኖር ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት የተመለከተ መሆኑን ገልጸዋል።