ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮን ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮን አግኝቼ፤ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ ለተሻለ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ያሉ እድሎች እና አፍሪካን ቀጣይ የሚመራ ትውልድን ማብቃት ላይ በጋራ በምንሰራበት አውድ ዙሪያ ውይይት አድርገናል ብለዋል።