የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፤የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፡-39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
እየተካሄደ የሚገኘውን 39ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ አስመልክቶ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በዚህ ወቅት፥ የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ በርካታ ኮንፈረንሶችን የማስተናገድ አቅም ዳግም ያረጋገጠችበት መሆኑን ገልጸዋል።
ጉባኤው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗን ከማረጋገጥ ባለፈ የሀገሪቱን ገጽታ በማጉላት በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
ጉባኤው ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ገቢን በማሳደግ ረገድም ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
በጉባኤው የበርካታ ሀገራት መሪዎች እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸው፥ በጣም ውጤታማ በሆነ መልኩ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ” ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በህብረቱ መቀመጫ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።