ቀጥታ፡

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፦ 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ጉባኤው የሚካሄደው” ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

መሪዎቹ የሚመክሩት 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ላይ ውይይት በተደረገባቸው አጀንዳዎች ላይ ነው።

የውሃ ደህንነት እና የንጽህና፣ አጠባበቅ፣ የአጀንዳ 2063 ትግበራን እና አህጉራዊ ትስስር፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ የሰው ኃይል ልማት፣ ተቋማዊ እና የፋይናንስ ሪፎርሞች፣ ቀጣናዊ አጋርነት እና አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና ከአጀንዳዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ።

39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ እስከ ነገ ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም