ቀጥታ፡

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሃዋሳ ከተማ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ ፤ የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፡-በሀገር መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በሀዋሳ ከተማ እየተካሔደ ነው።

በውድድሩ ከተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ ከ302 በላይ ታዋቂ ወንድና ሴት አትሌቶች ተሳትፈዋል።


 

እንዲሁም ከመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ ከሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና ከአጎራባች ክልል ከተሞች ጭምር የተውጣጡና በጠቅላላ ቁጥራቸው ወደ 10 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው። 


 

በሥነ-ስርዓቱ ላይ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ፣ ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን፤ ከፍተኛ መኮንኖች፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነና የአስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም