39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 7/2018 (ኢዜአ)፦ 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ዛሬ እና ነገ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይጀመራል።
ጉባዔው የሚካሄደው፤ "ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነው።
የኢትዮጵያ ዐሻራ ከዓድዋ - እስከ አፍሪካ ኅብረት
መሪዎቹ የሚመክሩት 48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በሳምንቱ አጋማሽ በአዲስ አበባ በመደበኛ ስብስባው በተወያየባቸው አጀንዳዎች ላይ ነው።
በዚህም መሠረት፤ የውኃ ደኅንነት እና የንጽህና አጠባበቅ፣ የአጀንዳ 2063 ትግበራ እና አኅጉራዊ ትሥሥር፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ የሰው ኃይል ልማት፣ ተቋማዊ እና የፋይናንስ ሪፎርሞች፣ ቀጣናዊ አጋርነት እና አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና ከአጀንዳዎቹ መካከል ናቸው።
የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎችም በጉባዔው ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።