ቀጥታ፡

የኬፕ ቨርዴ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴ ማሪያ ፔሬራ ኔቪስ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2018 (ኢዜአ)፡- የኬፕ ቨርዴ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴ ማሪያ ፔሬራ ኔቪስ 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)  አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነትበሚል መሪ ሐሳብ ነገ በአዲስ አበባ ይጀመራል።

በጉባዔው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም