ቀጥታ፡

የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኡስማን ሶንኮ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤የካቲት 6/2018(ኢዜአ)፦የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኡስማን ሶንኮ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ በአዲስ አበባ ይጀመራል።

በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም