የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቲዎዶሮ ኦቢያግን ንጉኤማ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቲዎዶሮ ኦቢያግን ንጉኤማ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2018(ኢዜአ)፦የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቲዎዶሮ ኦቢያግን ንጉኤማ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ በአዲስ አበባ ይጀመራል።
በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።