የሞሮኮ ጠቅላይ ሚኒስትር አዚዝ አክሃኖች በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሞሮኮ ጠቅላይ ሚኒስትር አዚዝ አክሃኖች በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2018(ኢዜአ)፦የሞሮኮ ጠቅላይ ሚኒስትር አዚዝ አክሃኖች በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።