ቀጥታ፡

የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲመለከቱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2018(ኢዜአ)፦ የ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲመለከቱ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዎች፣ በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፣ በዘመናዊ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፣ የአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ገበያዎች ተደራሽነት ላይ የተመሰረተ ሥነ ምህዳር መገንባቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በስትራቴጂካዊ፣ ዘላቂነት ላይ ባተኮረ አመራር በመመራትና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ታዳሽ ኃይል፣ የዲጂታል መሠረተ ልማትን ማስፋፋትና የተሻሻለ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ ሰፋፊ ሥራዎች መሰራታቸውንም ገልጿል።

በተጨማሪም የሰለጠነ የሰው ኃይል በግብርና፣ በማምረቻው፣ በኢ-ኮሜርስ፣ በማዕድንና ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችን በማጠናከርና የአፍሪካን የጋራ ብልጽግና በማሳደግ ላይ የተሰሩ ስራዎች ማቅረቧንም አስታውቋል፡፡

39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።

የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች https://linktr.ee/ENADigital

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም