ሁለተኛው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
ሁለተኛው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/ 2018(ኢዜአ)፦ ሁለተኛው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።
ጉባኤው የጣሊያን-አፍሪካ ግንኙነት በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብሮች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ ነው፡፡
ጉባኤው በአዲስ አበባ መካሔዱ ኢትዮጵያ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ያላትን አቅም እንደሚያሳይ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ 39ኛውን የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ እና የጣሊያን አፍሪካ ጉባዔን ለማስተናገድ ተዘጋጅታ እንግዶቿን እየተቀበለች ትገኛለች።
የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተቋማት ኃላፊዎች አዲስ አበባ ይገኛሉ።
የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ በአፍሪካ አህጉር ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው ነው።