አጀንዳ 2063: የ50 ዓመቱ የአፍሪካ እቅድ - ኢዜአ አማርኛ
አጀንዳ 2063: የ50 ዓመቱ የአፍሪካ እቅድ
.አጀንዳ 2063 ‘የምንፈልጋትን አፍሪካ ‘ በሚል መሪ ሀሳብ አፍሪካ ለ50 ዓመት (ከእ.አ.አ 2013 እስከ 2063) የምትመራበትን እቅድ የያዘ ማዕቀፍ ነው።
.አጀንዳው ለመጀመሪያ ጊዜ ውይይት የተደረገበት እ.አ.አ በ2013 በአዲስ አበባ በተካሄደው 21ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ(ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የተከበረበት ነው)።
.አጀንዳ 2063 እ.አ.አ በ2015 በአዲስ አበባ በተካሄደው 24ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ውይይት ተደርጎበት አባል አገራቱ አጽድቀውታል።
.የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት(የአሁኑ አፍሪካ ሕብረት) አፍሪካ ከአፓርታይድ ስርዓት ለማላቀቅና የፖለቲካ ነጻነት እንድታገኝ ሲያደርግ የነበረው ትግል ለአጀንዳ 2063 አጀንዳ መጠንሰስ ምክንያት እንደሆነ ይገለጻል።
.አጀንዳ 2063 በአፍሪካ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ የሆነ ልማት ማምጣት እንዲሁም በፓን አፍሪካኒዝምና የአፍሪካ ሕዳሴ ራዕይ ስር አንድነቷን የጠበቀች፣ የራስን እድል በራስ የምትወስን፣ነጻ የሆነች፣የተለወጠችና የበለጸገች አፍሪካ የመፍጠር ግብ እንዳለው የአፍሪካ ሕብረት በድረ ገጹ ላይ ያሰፈረው መረጃ ያሳያል።
.አጀንዳ 2063 የአፍሪካን ሁሉን አቀፍና ዘላቂ የልማት ግቦችን ያሳካል ተብሎ የታመነበት የአህጉሪቷ ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ ሲሆን፤አፍሪካን በዓለም መድረክ ተጽእኖ ፈጣሪ የማድረግ ራዕይ ያለው ነው።
አጀንዳ 2063 ሰባት ግቦች ሳይሆን ሰባት አላማዎች፣20 ግቦችና 15 ፕሮጀክቶች ያሉት ነው
የአጀንዳ 2063 ሰባት አላማዎችና ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫዎች
አጀንዳ 2063 ‘የምንፈልጋትን አፍሪካ ‘ በሚል መሪ ሀሳብ አፍሪካ ለ50 ዓመት (ከእ.አ.አ 2013 እስከ 2063) የምትመራበትን እቅድ የያዘ ማዕቀፍ ነው።
አጀንዳ 2063 ሰባት አላማዎችና ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫዎች አሉት።
እነሱም፦
1. ሁሉን አቀፍ በሆነ እድገትና ዘላቂ ልማት የበለጸገች አፍሪካን መፍጠር
2. በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤዎችና በአፍሪካ ሕዳሴ ራዕይ አማካኝነት የተሳሰረችና ፖለቲካዊ አንድነት ያላት አህጉርን እውን ማድረግ
3. አፍሪካን መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ የሰብአዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት የሚከበርባት፣ ፍትሕ የነገሰባትና ዴሞክራሲያዊ አህጉር ማድረግ
4 .ሰላሟንና አንድነቷን የጠበቀች አፍሪካን መፍጠር
5.ጠንካራ የባህል ማንነት፣ የጋራ ቅርስና እሴቶች ያሏት እንዲሁም ጠንካራ ማህበረሳባዊ የሞራል መሰረት የፈጠረች አፍሪካን ማየት
6. አፍሪካ ልማቷ ዜጎችን ማዕከል ያደረገ፣ የአፍሪካን ሕዝብ በተለይም የወጣቶችና ሴቶችን አቅም የሚጠቀምና ለሕጻናት ክብካቤ ትኩረትን የሰጠ እንዲሆን ማድረግ
7. ጠንካራ፣ አንድነቷን የጠበቀች፣ የማትበገርና በዓለም መድረክ ተጽእኖ ፈጣሪና አጋር የሆነች አፍሪካን መፍጠር ናቸው።
የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በአጀንዳ 2063 አፈጻጸም ትግበራ ላይ እንደሚመክር የህብረቱ መረጃ ያመለክታል።