ቀጥታ፡

የሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጠቅላይ ሚኒስትር አሜሪኮ ዲኦሊቬራ ዶስ ራሞስ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጠቅላይ ሚኒስትር አሜሪኮ ዲኦሊቬራ ዶስ ራሞስ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም