የናሚቢያ ፕሬዝደንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይቷ(ዶ/ር) አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የናሚቢያ ፕሬዝደንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይቷ(ዶ/ር) አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የናሚቢያ ፕሬዝደንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይቷ(ዶ/ር) በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።
በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።