የካሜሮን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ(ዶ/ር) አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የካሜሮን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ(ዶ/ር) አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የካሜሮን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ዲዮን ንጉቴ(ዶ/ር) በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።
በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።