ቀጥታ፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ከአፍሪካ መሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም እንዲሁ።

39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም