ቀጥታ፡

የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ) ፦ የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል።

በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም