ቀጥታ፡

የሲሼልስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ፒሌ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የሲሼልስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ፒሌ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል።

በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም