የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጄ ቶውዴራ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጄ ቶውዴራ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጄ ቶውዴራ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።
በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።