ቀጥታ፡

የኮትዲቯር ምክትል ፕሬዚዳንት ቲዬሞኮ ሜይሊየት ኮኔ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ) የኮትዲቯር ምክትል ፕሬዚዳንት ቲዬሞኮ ሜይሊየት ኮኔ 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(/) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

በጉባዔው የሚሳተፉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም