የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።
በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።