ቀጥታ፡

የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም የአፍሪካ መዲና ወደሆነችው አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም