የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀሲካ አሊፖ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀሲካ አሊፖ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀሲካ አሊፖ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንቷ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።