ቀጥታ፡

የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2018(ኢዜአ)፦ የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አቀባበል አድርገውላቸዋል።

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

በጉባኤው የሚሳተፉ መሪዎችም ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም