ቀጥታ፡

ማኅበራቱ በጠቅላላ ምርጫው የዜጎችን ተሳትፎ ለማጎልበት እየሠሩ እንደሚገኙ ገለፁ

ሐዋሳ፤ የካቲት 5/2018 (ኢዜአ)፡- በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ለማጎልበት እየሠሩ መሆናቸውን የመምህራን ማኅበራት አስታወቁ።


 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አማኑኤል ጳውሎስ እንዳሉት፤ ዜጎች በምርጫው ዴሞካራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲሳተፉ የመራጮችና የሥነ-ዜጋ ትምህርት ለመስጠት ማኅበሩ ዝግጅት ማጠናቀቁን ለኢዜአ አረጋግጠዋል።


 

የሲዳማ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ኢያሱ ፍቅሬ በበኩላቸው፤ መምህራን በማኅበረሰቡ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ተጠቅመው ዜጎች በምርጫው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ከወዲሁ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።


 

ማኅበሩ የሲቪክ ማኅበር እንደመሆኑ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲዊና ሠላማዊ እንዲሆን ከምርጫ ቦርድ ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑን ያስገነዘቡት ደግሞ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ናቸው።

መምህራን ምርጫው ጤናማ ሂደት እንዲኖረው ራሳቸው በመሳተፍም ሆነ ማኅበረሰቡን በማንቃት የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክቶችን እያስተላለፍን ነው ብለዋል፡፡

ከፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ የሆኑ መምህራን በሀገር አቀፍ ደረጃ በታዛቢነት አንዲሳተፉ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም