የመራጮች ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን ወደ የካቲት 28 ተራዘመ - ኢዜአ አማርኛ
የመራጮች ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን ወደ የካቲት 28 ተራዘመ
አዲስ አበባ፤የካቲት 5/2018 (ኢዜአ)፡-የመራጮች ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን ወደ የካቲት 28 መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫው ዙርያ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በምርጫ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ የካቲት 7 ለማከናወን ታቅዶ እንደነበር አስታውሰዋል።
ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚከናወኑ ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው ምዝገባው ወደ የካቲት 28 መራዘሙን አስታውቀዋል።
ጥር 1 ቀን 2018 ዓም የተጀመረው የእጩዎች ምዝገባ በፓርቲዎች ጥያቄ መሰረት እስከ 16 መራዘሙን ተናግረዋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 42 ተፎካካሪ ፓርቲዎች በተናጠል፣15 ፓርቲዎች ደግሞ በሁለት ጥምረትና በአንድ ግንባር ለመፎካከር መመዝገባቸውንም እንዲሁ።
ኢትዮጵያ በወሳኝ የምርጫ ወቅት ላይ በመሆኗ ለስኬታማነቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የቦርድ ሰብሳቢዋ ለኢዜአ መግለጻቸው ይታወቃል።
ከአጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ17 ሺህ ያህሉ የዲጂታል የመራጮች ምዝገባን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም መግለጻቸውም ይታወቃል።