ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ ፉልሃምን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶዋን ሴሜንዮ፣ ኒኮ ኦራይሊ እና አርሊንግ ሃላንድ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ማንችስተር ሲቲ በተጋጣሚው ላይ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።

ውጤቱን ተከትሎ በውድድር ዓመቱ 16ኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ሲቲ በ53 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ሶስት ዝቅ አድርጓል።

ውሃ ሰማያዊዎቹ በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝተዋል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፉልሃም በ34 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።በሊጉ ተከታታይ ሽንፈቱንም አስተናግዷል።

የማንችስተር ሲቲው አጥቂ አርሊንግ ሃላንድ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ወደ 22 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቱን አጠናክሯል።

በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ-ግብር አስቶንቪላ ብራይተንን በታይሮን ሚንግስ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል። ውጤቱን ተከትሎ ቪላ ነጥቡን ወደ 50 ከፍ በማድረግ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ብራይተን በ31 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ኖቲንግሃም ፎረስት እና ዎልቭስ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም