የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሶማኒ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሶማኒ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2018(ኢዜአ)፦ የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሶማኒ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተያያዘ ዜና የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት መሐመድ ጃሎው እና የሌሴቶው ንጉስ ሌትሴ ሳልሳዊ በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።