ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2018 (ኢዜአ)፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፤ዛሬ የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን ተቀብዬ በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

ውይይቱ በዐበይት ዘርፎች ለረዥም ዘመናት የዘለቀውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ትስስር በማስፋት ዙሪያ መምከራቸውን ጠቁመዋል።

እንዲሁም የወል ፍላጎቶቻችን በሆኑ ቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራችንን በማጠናከር ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም