ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ከፉልሃም ጋር ጨዋታውን ያከናውናል 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4 /2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። 

በኢትሃድ ስታዲየም ማንችስተር ሲቲ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ፉልሃምን ያስተናግዳል። 

ማንችስተር ሲቲ በ50 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ፉልሃም በ34 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በ25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 በማሸነፍ በዋንጫ ፉክክሩ የቆየበትን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። 

ውሃ ሰማያዊዎቹ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ሶስት ዝቅ ያደርጋሉ። 

ባለፉት ሁለት የሊጉ ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደው ፉልሃም ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። 

በሌላኛው መርሐ-ግብር ሰንደርላንድ ከሊቨርፑል ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ በስታዲየም ኦፍ ላይት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሰንደርላንድ በ36 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ሊቨርፑል በ39 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱም ቡድኖች በ25ኛ ሳምንት ካስተናገዱት ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ። 

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርገው ፉክክር ከዛሬው ጨዋታ ሶስት ነጥብ ያስፈልገዋል።

አስቶንቪላ ከብራይተን፣ ክሪስታል ፓላስ ከበርንሌይ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ከዎልቭስ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም