ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች በነበሩት አማን ፍሰሃ ጽዮን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች በነበሩት አማን ፍሰሃ ጽዮን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች በነበሩት አማን ፍሰሃ ጽዮን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በሀዘን መልዕክታቸው የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች በነበሩት አማን ፍሰሃ ጽዮን ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ሃዘን እየገለጽኩ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል።
ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር ሲሉም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።