ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኢቢኤስ ቴሌቭዥን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍሥሐ ጽዮን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኢቢኤስ ቴሌቭዥን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍሥሐ ጽዮን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኢቢኤስ ቴሌቭዥን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍሥሐ ጽዮን ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት የኢቢኤስ ቴሌቭዥን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍሥሐ ጽዮን በማረፉ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡
አማን ለኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ዕድገት ወሳኝ ሚና ከነበራቸው አንዱ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ባለፈች ጊዜ ሁሉ የሚጠበቅበትን አድርጓል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈጣሪ ነፍሱን በሰላም ያሳርፋት ሲሉም ሀዘናቸውን ገልጸዋል፡፡