የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢቤኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች የነበሩት አቶ አማን ፍስሃጽዮን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ሚዲያ ዕድገት ስኬት የማይተካ ሚና የተጫወቱት አቶ አማን፤ የታላቅ ራዕይ ባለቤትና ብርቱ ሰው እንደነበሩም ኢቢኤስ ባወጣው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በአቶ አማን ፍስሃጽዮን ህልፈት የተሰማውን ሃዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡