6ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም አውደ ጥናት መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
6ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም አውደ ጥናት መካሄድ ጀመረ
ሆሳዕና፤ የካቲት 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያዘጋጀው 6ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም አውደ ጥናት በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
አውደ ጥናቱ "ሀይማኖት ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለአብሮነት'' በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ የጀመረ ሲሆን የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው፡፡
በመድረኩም የሀይማኖት ተቋማት እና የሀይማኖት መሪዎች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና፣ ከብዝሃነት አያያዝና ከሰላም ግንባታ አኳያ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትና ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ነው የተመላከተው፡፡
በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የሰላም ሚኒስቴር ተወካዮችን ጨምሮ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከፍተኛ አመራሮችና የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ነው፡፡