ቀጥታ፡

48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2018(ኢዜአ)፦ 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ስብሰባው “ዘላቂ የውሃ ኑረትና ንጽህና ስርዓት ለአጀንዳ 2063 ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ ይደረጋል።

የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶችና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በስብሰባው የሚሳተፉ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

ምክር ቤቱ በጥር ወር 2018 ዓ.ም 51ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ በተወያየባቸው አጀንዳዎች ላይ ምክክር ያደርጋል።

የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ እስከ ነገ ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም