ቼልሲ ነጥብ ጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
ቼልሲ ነጥብ ጥሏል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቼልሲ እና ሊድስ ዩናይትድ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆአኦ ፔድሮ በ24ኛው ደቂቃ እና ኮል ፓልመር በ58ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ቼልሲ 2 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር።
ሉካስ ንሜቻ በ67ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት እና ኖህ ኦካፎር በ73ኛው ደቂቃ በጨዋታ የሊድስን የአቻነት ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ባለሜዳው ቼልሲ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ፉክክሩ ወሳኝ ነጥብ ጥሏል።
በሌላኛው ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ በማሊክ ታው እና ጃኮብ ራምሴይ ግቦች ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 1 አሸንፏል።
አርቺ ግሬይ ለቶተንሃም ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ቦርንማውዝ ኤቨርተንን 2 ለ 1 አሸንፏል።