የህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ነገ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦ 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የሚሳተፉ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።
የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።