የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው።
የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አታፍም ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ በረኦ ሀሰን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጉባኤው አስቀድሞ የካቲት 4 እና 5 ቀን የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 48ኛው መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል።
የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የሚል መሪ ሃሳብ ተሰጥቶታል።