ቀጥታ፡

የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018(ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር አባላት ተገኝተዋል።


 

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሪ መልዕክትነት ተሰይሟል።

የብልፅግና ፓርቲ የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶ  የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም