የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018 (ኢዜአ)፦ የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶችን ዛሬ ማለዳ ጎብኝተዋል።
የውድድር ዋና ዳይሬክተሩ ፒርስ ኦክላጋን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ግብዣ መሰረት ለጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘው የአደይ አበባ ዓለም አቀፍ የመለማመጃ ትራክ እና የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚን ጎብኝተዋል።
ፌዴሬሽኑ በቀጣይ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና የአንድ ቀን ውድድሮች (One day meeting) ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት የሚያደርገው ዝግጅት የዳይሬክተሩ ጉብኝት ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የስፖርት ዲፕሎማሲ ግንኙነትን የማጠናከር ፋይዳ እንዳለውም የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ፣ ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና ከፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።